የግላዊነት ፖሊሲ
DearMamma መተግበሪያ እና ድረ ገጽ
1. መግቢያ
እባክዎን ሁለቱም በስዊዘርላንድ በሚገኘው DEAR ፋውንዴሽን ("DEAR ፋውንዴሽን"፣ "እኛ"፣ "እኛ" ወይም "የእኛ") የሚንቀሳቀሱትን DEARMamma የጡት ካንሰር ግንዛቤ መተግበሪያን ("DEARMamma App"፣ "መተግበሪያ"፣ "አገልግሎት") እና/ወይም ተጓዳኝ የሆነውን DEARMamma ድረ ገጽን ("ድረ ገጽ"፣ "አገልግሎት")፣ ከመጠቀምዎ በፊት የግላዊነት ፖሊሲውን ("ፖሊሲ") በጥንቃቄ ያንብቡ። የ DEARMamma መተግበሪያ እና/ወይም DearMamma ድረ ገጽ አጠቃቀምዎ ፖሊሲው መቀበልዎ እና ማክበርዎ ላይ የተመሠረተ ነው። ፖሊሲው ለሁሉም ጎብኚዎች፣ ተጠቃሚዎች እና ሌሎች መተግበሪያውን እና/ወይም ድረ ገጹን ለሚጠቀሙ ሰዎች ተፈጻሚ ይሆናል። መተግበሪያውን እና/ወይም ድረ ገጹን በመጠቀም፣ በዚህ ፖሊሲ ለመገዛት ይስማማሉ። በማንኛውም የፖሊሲው ክፍል ካልተስማሙ አገልግሎቱን እንዲያገኙ አይፈቀድልዎትም።
The DEAR Foundation Switzerland - DearMamma መተግበሪያን እና ድረ ገጹን እንደ ነፃ አገልግሎት አዘጋጅቷል። ይህ አገልግሎት በ DEAR ፋውንዴሽን ያለ ምንም ወጪ የሚቀርብ ሲሆን እንዳለ ጥቅም ላይ እንዲውል የታሰበ ነው። አገልግሎታችንን ለመጠቀም ከመረጡ፣ ከዚህ ፖሊሲ ጋር በተያያዘ መረጃ እንዲሰበሰብ እና ጥቅም ላይ እንዲውል ይስማማሉ። የምንሰበስበው የግል መረጃ አገልግሎቱን ለማቅረብ እና ለማሻሻል ጥቅም ላይ ይውላል። በዚህ ፖሊሲ ውስጥ እንደተገለጸው ብቻ ነው የእርስዎን መረጃ የምንጠቀመው እና የምናጋራው።
አገልግሎታችንን ለመጠቀም ከመረጡ፣ በዚህ ፖሊሲ መሰረት መረጃ እንዲሰበሰብ እና ጥቅም ላይ እንዲውል ይስማማሉ። DEAR ፋውንዴሽን ለመረጃ አሰባሰብ እና መረጃን ፕሮሰስ ለማድረግ ኃላፊነት ያለበት ሲሆን የግል መረጃዎችን
- በስዊስ ፌዴራል የመረጃ ጥበቃ ህግ ("FADP") እና
- በ 25/05/2018 EU አጠቃላይ የመረጃ ጥበቃ ደንብ ("GDPR") መሰረት ፕሮሰስ ያደርጋል።
የምንሰበስበው የግል መረጃ አገልግሎቱን ለማቅረብ እና ለማሻሻል ጥቅም ላይ ይውላል። በዚህ ፖሊሲ ውስጥ በተገለጸው መሰረት ብቻ የእርስዎን መረጃ እንጠቀማለን እንዲሁም ለሶስተኛ ወገኖች እናጋራለን።
ኃላፊነት ያለው አካል
The DEAR Foundation Switzerland
Obfelderstrasse 41a
8910 Affoltern am Albis
ስዊዘሪላንድ
የኢሜል አድራሻ:
2. የግል መረጃ አሰባሰብ እና አጠቃቀም
የግል መረጃ ማለት እንደ ስም፣ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር እና ኢ-ሜይል ያሉ ከአንድ የተወሰነ ወይም ተለይቶ ሊታወቅ የሚችል ሰው ጋር የሚዛመድ ማንኛውም መረጃ ነው። መረጃ ፕሮሰስ የሚደረግባቸው ሁለቱም የተፈጥሮ እና ህጋዊ ሰዎች ይነካሉ።
2.1 ኩኪዎች
የሞባይል መሳሪያዎች እና ድረ ገጾች ኩኪዎች እና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች፣ በተለምዶ ስም ሳይገለጽ ጥቅም ላይ የሚውሉ ልዩ መለያዎች የሆኑ አነስተኛ መጠን ያለው ውሂብ ያላቸው ፋይሎች ናቸው። እነዚህ እርስዎ ከሚጎበኟቸው ድር ገጾች ወደ አሳሽዎ ይላኩ እና በመሳሪያዎ ውስጣዊ ማህደረ ትውስታ ላይ ይቀመጣሉ።
አገልግሎታችን ኩኪዎችን ይጠቀማል። በተጨማሪም፣ መተግበሪያው መረጃ ለመሰብሰብ እና አገልግሎቶቻቸውን ለማሻሻል ኩኪዎችን የሚጠቀሙ የሶስተኛ ወገን ኮድ እና ላይብራሪዎችን ሊጠቀም ይችላል።
መርጦ-መውጫ አማራጭ፦ ሁልጊዜ ለኩኪዎች የተሰጠን ፈቃድ የመሻር ወይም መረጃዎ በኩኪዎች ጥቅም ላይ እንዳይውል የመቃወም አማራጭ አለዎት። የአሳሽዎን ወይም በመሳሪያዎ ላይ ያሉትን ኩኪዎች አጠቃቀም በማጥፋት ይህንን ማድረግ ይችላሉ።
ፍቃድዎን ለመሻር ወይም ኩኪዎችን ላለመቀበል ከመረጡ፣ የዚህን አገልግሎት አንዳንድ ክፍሎች መጠቀም ላይችሉ ይችላሉ።
2.2. DearMamma መተግበሪያ
ተጠቃሚው የ DearMamma መተግበሪያን ስሙ ሳይታወቅ የመጠቀም ወይም መተግበሪያውን ለግል የማበጀት አማራጭ አለው።
2.2.1. በጡት ካንሰር ምርመራ ወቅት የግል መረጃን በግልፅ ማከማቸት
በጡት ካንሰር ምርመራ ወቅት የሚሰበሰበው ግላዊ መረጃ፣ መተግበሪያውን በሚጠቀሙበት ወቅት የሚገቡ እና/ወይም የሚቀመጡ (ማስታወሻዎች፣ ፎቶዎች፣ ኦዲዮ) ሁል ጊዜ በአካባቢው በተጠቃሚው ስልክ ላይ ይከማቻሉ። DEAR ፋውንዴሽን እና/ወይም ማንኛውም ሶስተኛ ወገኖች የዚህ አይነት መረጃ መዳረሻ የላቸውም።
2.2.2. ለሶስተኛ ወገኖች የሚጋራ የግል መረጃ
በጡት ካንሰር ምርመራ ወቅት ከተሰበሰበው የግል መረጃ (እባክዎን የዚህን ፖሊሲ 2.2.1 ለዝርዝር ይመልከቱ)፣ ይህም በግል መሳሪያዎ ላይ በአካባቢ ከተከማቸው በተጨማሪ፣ እኛ ለሶስተኛ ወገኖች የምናጋራቸው የግል መረጃዎችም አሉ። በእንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ውስጥ፣ ሁሉንም የህግ መስፈርቶች እናከብራለን እንዲሁም በዚህ የግላዊነት ፖሊሲ ውስጥ በተገለፀው መሰረት ብቻ መረጃውን እንጠቀማለን፦
ምንም የአካባቢ ታሪክ እና ምንም የእንቅስቃሴ መገለጫዎች የሉም
የአካባቢ ታሪክ ወይም ጥቅም ላይ የዋሉትን መሳሪያዎች እና/ወይም የተጠቃሚዎቻቸውን የእንቅስቃሴ መገለጫ ለመፍጠር የአካባቢ መረጃ ፕሮሰስ አልተደረገም።
የፌስቡክ ሶፍትዌር ልማት ኪት (Facebook Software-Development Kit (SDK)
መተግበሪያችን የማህበራዊ ኔትዎርክ ፌስቡክ የሆነውን የፌስቡክ ሶፍትዌሮች እድገት ኪትን ("Facebook SDK") ይጠቀማል። ኦፕሬተሩ Facebook Inc, 1601 S. California Ave, Palo Alto, CA 94304, USA ነው። በአውሮፓ ላሉ ተጠቃሚዎች ኦፕሬተሩ Facebook Ireland Ltd, 4 Grand Canal Square, Grand Canal Harbour, Dublin 2, Ireland ነው።
በ DEAR ፋውንዴሽን በፌስቡክ ላይ የሚቀመጥ መተግበሪያ ለሆነው ለ DearMamma የፌስቡክ ማስታወቂያዎችን ("Facebook Adsን") ውጤታማነት ለመለካት የፌስቡክ SDK ጥቅም ላይ ይውላል። የፌስቡክ SDK በመጨረሻው መሣሪያ ላይ ማስታወቂያዎችን ለማሳየት መረጃን ለማስተላለፍ እንደ በይነገጽ ያገለግላል። በተጨማሪም፣ በመተግበሪያው ውስጥ የመረጃ ትንታኔዎችን እና የተጠቃሚ ባህሪን ይከታተላል።
መተግበሪያችን ጎግል አናሌቲክስን ይጠቀማል። ኦፕሬተሩ Google LLC, 1600 Amphitheatre Parkway, Mountain View, CA 94043, USA ("Google") ነው። አውሮፓ ውስጥ ላሉ ተጠቃሚዎች ኦፕሬተሩ Google Ireland Limited, Gordon House, Barrow Street, Dublin 4, Ireland ነው።
የሞባይል ጉግል አናሌቲክስ በመተግበሪያችን የተጠቃሚዎችን ማግኛ እና ተሳትፎን ይለካል እንዲሁም ያሻሽላል።
2.3. DearMamma ድህረ ገጽ
ድረ ገጻችን የማህበራዊ ኔትዎርክ ፌስቡክ የሆነውን Facebook Pixel ይጠቀማል። ኦፕሬተሩ Facebook Inc, 1601 S. California Ave, Palo Alto, CA 94304, USA ነው። በአውሮፓ ውስጥ ላሉ ተጠቃሚዎች ኦፕሬተሩ Facebook Ireland Ltd, 4 Grand Canal Square, Grand Canal Harbour, Dublin 2, Ireland ነው።
Facebook Pixel እንደ የ DearMamma ድረ ገጽ ጎብኚ የፌስቡክ ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማሳየት ያገለግላል። የፌስቡክ ማስታወቂያዎችን ለማሳየት የዒላማ ቡድን እንደሆኑ ይወስድዎታል። በ Facebook Pixel እገዛ የፌስቡክ ማስታወቂያዎችን ለስታቲስቲክስ እና ለገበያ ጥናት ዓላማዎች ውጤታማነት መከታተል እንችላለን።
ድረ ገጻችን ጉግል አናሌቲክስን ይጠቀማል። ኦፕሬተሩ Google LLC, 1600 Amphitheatre Parkway, Mountain View, CA 94043, USA ("Google") ነው። አውሮፓ ውስጥ ላሉ ተጠቃሚዎች ኦፕሬተሩ Google Ireland Limited, Gordon House, Barrow Street, Dublin 4, Ireland ነው።
የድረ ገጾች Google Analytics የተጠቃሚውን ማግኛ እና ከድረ ገጻችን ጋር ያለውን ግንኙነት ይለካል እንዲሁም ያሻሽላል።
Pinterest-Tag Conversation-Tracking
የድረ ገጻችን የ Pinterest-Tag ልወጣ-መከታተያን ("Pinterest-Tag") ይጠቀማል። ኦፕሬተሩ Pinterest Inc, 505 Brannan Street San Francisco, CA 94107 United States ነው። አውሮፓ ውስጥ ላሉ ተጠቃሚዎች ኦፕሬተሩ Pinterest Europe Ltd., Palmerston House, 2nd Floor, Fenian Street, Dublin 2, Ireland ነው።
Pinterest-Tag የድረ ገጽ ተጠቃሚዎችን እና የ ፒንተረስት ማስታወቂያን ካዩ በኋላ የሚወስዷቸውን እርምጃዎች ለመከታተል የሚያስችል ኮድ ቅንጣቢ ነው። በተጨማሪም፣ የ ፒንተረስት ማስታወቂያን ውጤታማነት ይለካል።
3. ሌሎች ድረ ገጾች እና ማህበራዊ ሚዲያ
መተግበሪያው በ DEAR ፋውንዴሽን ያልተያዙ ወይም ቁጥጥር የማይደረጉባቸው የሶስተኛ ወገን ድረ ገጾች ወይም አገልግሎቶች ማስፈንጠሪያዎችን ሊይዝ ይችላል። የ DEAR ፋውንዴሽን በይዘቱ፣ በግላዊነት ፖሊሲዎች፣ ወይም ለማንኛውም የሶስተኛ ወገን ድረ ገጾች ወይም አገልግሎቶች ልምምዶች ላይ ቁጥጥር የለውም እንዲሁም ምንም አይነት ኃላፊነት አይወስድም። በተጨማሪም DEAR ፋውንዴሽን ለደረሰው ወይም ደርሷል ተብሎ ለቀረበ ጉዳት ወይም ኪሳራ ወይም በማናቸውም እንደዚህ ባሉ ድረ ገጾች ወይም አገልግሎቶች ላይ በሚገኙ ማናቸውም ይዘቶች፣ እቃዎች ወይም አገልግሎቶች ከመጠቀም ወይም ከመተማመን ጋር በተያያዘ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ኃላፊነት እንደማይወስድ ወይም ተጠያቂ እንደማይሆን አውቀው ተስማምተዋል።
በመተግበሪያው እና/ወይም በድረ ገጹ ጥቅም ላይ በዋሉ ወይም ከመተግበሪያው እና/ወይም ከድረ ገጹ ጋር የተገናኙ አገልግሎቶች፦
- ኢንስታግራም የሚንቀሳቀሰው በ Instagram Inc., 1601 Willow Road, Menlo Park, CA, 94025, USA ነው። ባለቤት ኩባንያ Facebook, 1 Hacker Way, Menlo Park, CA 94025, USA ነው። ድረ ገጽ፦ https://www.instagram.com እና የግላዊነት ፖሊሲ፦ https://instagram.com/about/legal/privacy.
- ፌስቡክ የሚንቀሳቀሰው በ Facebook Ireland Ltd., 4 Grand Canal Square, Grand Canal Harbour, Dublin 2, Ireland (ለአውሮፓ) እና Facebook, 1 Hacker Way, Menlo Park, CA 94025, USA (ከአውሮፓ ውጪ) ነው። ድረ ገጽ፦ https://www.facebook.com እና የግላዊነት ፖሊሲ፦https://www.facebook.com/about/privacy።
- ፒንተረስት (Pinterest) የሚንቀሳቀሰው በ Pinterest Inc.፣ 635 High Street፣ Palo Alto፣ CA፣ 94301፣ USA ነው። ድረ ገጽ፦ https://www.pinterest.com እና የግላዊነት ፖሊሲ፦https://about.pinterest.com/de/privacy-policy።
- ዩቱብ (YouTube) የሚንቀሳቀሰው በ Google Ireland Limited፣ Gordon House፣ Barrow Street፣ Dublin 4፣ Ireland (ለአውሮፓ) እና Google LLC፣ 1600 Amphitheatre Parkway፣ Mountain View፣ CA 94043፣ USA (ከአውሮፓ ውጪ) ነው። ድረ ገጽ፦ https://www.youtube.com እና የግላዊነት ፖሊሲ፦https://policies.google.com/privacy።
- Google API Fontsየሚንቀሳቀሰው በ Google Ireland Limited, Gordon House, Barrow Street, Dublin 4, Ireland (ለአውሮፓ)፣ እና Google LLC, 1600 Amphitheatre Parkway, Mountain View, CA 94043, USA (ከአውሮፓ ውጪ) ነው። ድረ ገጽ፦ https://fonts.google.com እና የግላዊነት ፖሊሲ፦https://policies.google.com/privacy
መርጦ-መውጫ አማራጭ፦ ሁል ጊዜ የሌሎችን ድረ ገጾች እና/ወይም ከላይ የተጠቀሱትን የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን አገልግሎት ለመጠቀም የተሰጠ ፈቃድን የመሻር ወይም የመቃወም አማራጭ አለዎት። ይህንን ለማድረግ፣ እባክዎን ከላይ የተጠቀሱትን ድረ ገጾች እና/ወይም የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን ይጎብኙ እና መርጠው ይውጡ።
በሚከተሉት አገልግሎቶች ተጠቃሚው የድረ ገጻችንን ማስፈንጠሪያ በፈቃደኝነት ለሌሎች ተጠቃሚዎች ማጋራት ይችላል፦
4. የመተግበሪያ መደብሮች
DearMamma መተግበሪያን ከተወሰኑ የኦንላይን መድረኮች ("App Stores") ላይ ማውረድ ይችላል። በዚህ አውድ ውስጥ፣ የግል የግላዊነት ፖሊሲያቸው ይሠራል። ጥቅም ላይ የዋሉ አገልግሎቶች፦
- Apple App Store: https://www.apple.com/de/ios/app-store/፣
የግላዊነት ፖሊሲ: https://www.apple.com/privacy/privacy-policy/። - Google Play፦ https://play.google.com/store/apps?hl=de፣
የግላዊነት መመሪያ፦ https://policies.google.com/privacy።
5. ብቅ ባይ መልዕክቶች
በተጠቃሚው ፈቃድ፣ የ DearMamma መተግበሪያ የተጠቃሚውን ብቅ ባይ መልዕክቶች መላክ ይችላል። እነዚህ መልዕክቶች መተግበሪያውን በማይጠቀሙበት ጊዜ እንኳን ለተጠቃሚው ሊታዩ ይችላሉ። ብቅ ባይ መልዕክቶችን መቀበል በተጠቃሚው መሣሪያ የማሳወቂያ ቅንብሮችን በመጠቀም በማንኛውም ጊዜ በተጠቃሚው ሊቀየር ይችላል።
6. የምዝግብ ማስታወሻ ውሂብ
የዚህ መተግበሪያ እና የድረ ገጽ አቅራቢ በራስ-ሰር መረጃን በአገልጋይ መዝገብ ማስታወሻ ፋይሎች ውስጥ ይሰበስባል እንዲሁም ያከማቻል። እነዚህ በቀጥታ ወደ እኛ የሚተላለፉ ናቸው።
ይህ የምዝግብ ማስታወሻ ውሂብ እንደ መሳሪያዎ የኢንተርኔት ፕሮቶኮል ("IP") አድራሻ፣ የመሳሪያ ስም፣ የስርዓተ ክወና ስሪት፣ አገልግሎታችንን ስንጠቀም የመተግበሪያው ውቅር፣ አገልግሎቱን እና ሌሎች ስታቲስቲክሶችን የተጠቀሙበት ሰዓት እና ቀን ያሉ መረጃዎችን ሊያካትት ይችላል።
7. አገልግሎት ሰጪዎች
በሚከተሉት ምክንያቶች የሶስተኛ ወገን ኩባንያዎችን እና ግለሰቦችን ልንቀጥር እንችላለን፦
- አገልግሎታችንን ለማመቻቸት እና ለማሻሻል፤
- አገልግሎቱን በእኛ ፈንታ ለማቅረብ፤
- ከአገልግሎት ጋር የተያያዙ አገልግሎቶችን ለማከናወን፤ ወይም
- አገልግሎታችን እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል ለመተንተን እንዲያግዘን።
በእኛ ምትክ የተሰጣቸውን ተግባራት ለማከናወን እነዚህ ሶስተኛ ወገኖች በዚህ ፖሊሲ 2.2.2 የተገለፀውን የእርስዎን የግል መረጃ ብቻ ማግኘት የሚችሉ እንደሆነ ለተጠቃሚዎች ማሳወቅ እንፈልጋለን። ነገር ግን፣ እነዚህ ኩባንያዎች እና ግለሰቦች የእርስዎን መረጃ የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው እናም መረጃውን ለሌላ ዓላማ እንዳይገልጹ ወይም እንዳይጠቀሙበት የተከለከሉ ናቸው።
8. ደህንነት
የእርስዎን የግል መረጃ ለእኛ ለማቅረብ ስላለዎት እምነት ዋጋ እንሰጣለን፣ ስለዚህ እሱን ለመጠበቅ በንግድ ተቀባይነት ያላቸውን መንገዶች ለመጠቀም እየጣርን ነው። ነገር ግን፣ ምንም አይነት በኢንተርኔት የሚደረግ ማስተላለፊያ ዘዴ ወይም የኤሌክትሮኒክስ ማከማቻ 100% ደህንነቱ የተጠበቀ አይደለም፣ እናም ፍጹም የሆነ ደህንነቱን ማረጋገጥ አንችልም።
9. የልጆች ግላዊነት
የመተግበሪያው እና የድረ ገጹ አገልግሎት ከ 18 ዓመት በታች የሆነን ሰው አያስተናግድም። እያወቅን ከ 18 ዓመት በታች ካሉ ልጆች በግል ማንነትን የሚለይ መረጃ አንሰበስብም። ከ 18 ዓመት በታች የሆነ ልጅ መረጃ እንደሰጠን ካወቅን፣ ወዲያውኑ ይህንን ከሰርቨሮቻችን እንሰርዛለን። እርስዎ ወላጅ ወይም አሳዳጊ ከሆኑ እና ልጅዎ መረጃ እንደሰጠን የሚያውቁ ከሆነ፣ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ እንድንችል እባክዎን ያነጋግሩን።
10. በዚህ የግላዊነት ፖሊሲ ላይ የሚደረጉ ለውጦች
ይህንን ፖሊሲ በማንኛውም ጊዜ ብቻችንን የመቀየር ወይም የመተካት መብታችን የተጠጠበቀ ነው። በዚህ ፖሊሲ ላይ የሚደረጉ ለውጦች ለተጠቃሚው ይነገራሉ። ለውጦቹ በዚህ ገጽ ላይ ከተለጠፉ በኋላ ወዲያውኑ ተፈጻሚ ይሆናሉ።
11. የተጠቃሚው መብቶች
በሚመለከታቸው የህግ መስፈርቶች መሰረት ተጠቃሚዎች መረጃቸውን በሚመለከት የሚከተሉት መብቶች አሏቸው፦ የመቃወም መብት፣ መረጃ የማግኘት መብት፣ መረጃን የመሰረዝ መብት፣ የማረም መብት፣ መረጃን የማስተላለፍ መብት እና ለተቆጣጣሪ ባለስልጣን ቅሬታ የማቅረብ መብት (EU አጠቃላይ የውሂብ ጥበቃ ደንብ)።
12. የመረጃ መሰረዝ
በህጋዊ መስፈርቶች መሰረት፣ ፕሮሰስ ለማድረግ የተሰጡ ፈቃዶች እንደተሻሩ ወይም ሥራ ላይ መዋል ካቆሙ በኋላ (ለምሳሌ፣ ይህን መረጃ ፕሮሰስ የማድረግ ዓላማ ሥራ ላይ መዋል አቁሟል እና/ወይም አያስፈልግም)፣ በእኛ ፕሮሰስ የተደረገ መረጃ ይሰረዛል።
13. ያግኙን
ስለ ፖሊሲያችን ማንኛውም አይነት ጥያቄዎች ወይም የሚፈልጉዋቸው ነገሮች ካሉዎት፣ በ እኛን ለማነጋገር አያመንቱ።
የመጨረሻው ዝመና፦ 22. ኤፕሪል 2021