ውሎች እና ግዴታዎች

1. መግቢያ

እባክዎን የ DearMamma የጡት ካንሰር ማስገንዘቢያ መተግበሪያን ("DearMamma መተግበሪያ"፣ "መተግበሪያ"፣ "አገልግሎት") እና/ወይም በስዊዘርላንድ በሚገኘው DEAR ፋውንዴሽን ("DEAR ፋውንዴሽን"፣ "እኛ"፣ "እኛ" ወይም "የእኛ") የሚተዳደር ተጓዳኝ የ DearMamma ድረ ገጽ ("ድረ ገጽ"፣ "አገልግሎት") ከመጠቀምዎ በፊት እነዚህን ውሎች እና ግዴታዎች ("ውሎች"፣"ውሎች እና ግዴታዎች") በጥንቃቄ ያንብቡ። እነዚህ ውሎች ከግላዊነት ፖሊሲ ጋር በእርስዎ እና በ DEAR ፋውንዴሽን ከአገልግሎቶች አጠቃቀምዎ ጋር በተያያዘ ህጋዊ አስገዳጅ ስምምነት ("ስምምነት") ይመሰርታሉ። የ DearMamma መተግበሪያ እና/ወይም የ DearMamma ድረ ገጽ መዳረሻዎ እና አጠቃቀምዎ እነዚህን ውሎች በመቀበልዎ እና በማክበርዎ ላይ የተመሰረተ ነው። እነዚህ ውሎች አገልግሎቱን ለሚያገኙ ወይም ለሚጠቀሙ ሁሉም ጎብኚዎች፣ ተጠቃሚዎች እና ሌሎችም ተፈጻሚ ይሆናሉ። አገልግሎቱን በማውረድ፣ በማግኘት ወይም በመጠቀም፣ በእነዚህ ውሎች ለመገዛት ይስማማሉ። በማንኛውም የውሉ ክፍል ካልተስማሙ አገልግሎቱን ማግኘት አይችሉም። መተግበሪያውን እና/ወይም ድረ ገጹን፣ የትኛውንም የመተግበሪያው አካል እና/ወይም ድረ ገጽ፣ ወይም የመተግበሪያውን እና/ወይም ድረ ገጹን የንግድ ምልክቶች በማንኛውም መንገድ መቅዳት ወይም ማሻሻል አልተፈቀደልዎትም። የመተግበሪያውን የምንጭ ኮድ ለማውጣት መሞከር አይፈቀድልዎትም፣ እንዲሁም አገልግሎቱን ወደ ሌሎች ቋንቋዎች ለመተርጎም ወይም ተመሳስይ ስሪቶችን ለማዘጋጀት መሞከር የለብዎትም። አገልግሎቱ ራሱ፣ እንዲሁም ሁሉም የንግድ ምልክቶች፣ የቅጂ መብት፣ የውሂብ ጎታ መብቶች እና ከሱ ጋር የተያያዙ ሌሎች የአዕምሮአዊ ንብረት መብቶችም የ DEAR ፋውንዴሽን ናቸው።

2. የመተግበሪያ እና የድረ ገጽ የተጠቃሚ ፖሊሲዎች

አገልግሎታችንን ለማሻሻል መተግበሪያ እና ድረ ገጽ እርስዎ የሰጡንን የግል መረጃ ያከማቻሉ እንዲሁም ፕሮሰስ ያደርጋሉ። የእርስዎን የግል መረጃ መሰብሰብን እና መጠበቅን በተመለከተ የግላዊነት ፖሊሲን እንጠቅሳለን። የስልክዎን እና የመተግበሪያውን እና/ወይም ድረ ገጹን ደህንነት መጠበቅ የእርስዎ ኃላፊነት ነው። ስለዚህ ስልክዎን jailbreak ወይም root እንዳያደርጉት እንመክራለን፣ ይህም በመሳሪያዎ ኦፊሴላዊ ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚጣሉ የሶፍትዌር ክልከላዎችን እና ገደቦችን የማስወገድ ሂደት ነው። ስልክዎን ለማልዌር/ቫይረሶች/ጎጂ ፕሮግራሞች ተጋላጭ ሊያደርገው ይችላል፣ የስልክዎን ደህንነት ባህሪያት ያበላሻል እንዲሁም መተግበሪያው በትክክል አይሠራም ወይም ጨርሶ አይሠራም ማለት ነው። የተወሰኑ የመተግበሪያው እና የድረ ገጹ ተግባራት መሳሪያዎ ንቁ የበይነመረብ ግንኙነት እንዲኖረው ይፈልጋሉ። ግንኙነቱ Wi-Fi፣ ወይም በእርስዎ (ሞባይል) አውታረ መረብ አቅራቢ የቀረበ ሊሆን ይችላል። የ Wi-Fi መዳረሻ ከሌለዎት እና/ወይም ምንም የሚቀርዎት የውሂብ ክፍያ ከሌለዎት፣ DEAR ፋውንዴሽን አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ ባለመሥራቱ ኃላፊነቱን አይወስድም። አገልግሎቱን Wi-Fi ካለው አካባቢ ውጭ እየተጠቀሙ ከሆነ፣ ከእርስዎ (የሞባይል) አውታረ መረብ አቅራቢ ጋር ያለዎት የስምምነት ውል አሁንም መሥራቱን እንደሚቀጥል ማስታወስ አለብዎት። በዚህም፣ አገልግሎቱን በሚያገኙበት ጊዜ፣ አቅራቢዎ ለግንኙነቱ ጊዜ የውሂብ ወጪ ወይም ሌላ የሶስተኛ ወገን ክፍያዎችን እንዲከፍሉ ሊያደርግ ይችላል። አገልግሎቱን በሚጠቀሙበት ጊዜ የውሂብ ዝውውርን ሳያጠፉ አገልግሎቱን ከቤትዎ አከባቢ (ማለትም ክልል ወይም አገር) ውጭ ከተጠቀሙ፣ የዝውውር ውሂብ ክፍያዎችን ጨምሮ ለማንኛውም ላሉ ክፍያዎች ኃላፊነቱን እየወሰዱ ነው። አገልግሎቱን እየተጠቀሙበት ላለው መሳሪያ ሂሳብ ከፋይ ካልሆኑ፣ እባክዎን አገልግሎቱን ለመጠቀም ከሂሳብ ከፋዩ ፈቃድ ተቀብለዋል እንደምናስብ ይወቁ። ህግ በሚፈቅደው መጠን፣ ለማንኛውም ችግር ወይም በአገልግሎቱ ላለመርካት ብቸኛ እና ብቸኛ መፍትሄ መተግበሪያውን ከመሳሪያዎ ማጥፋት እና ድረ ገጹን መጠቀም ማቆም እንደሆነ ተስማምተዋል። DEAR ፋውንዴሽን እና ተባባሪዎቹ፣ ግብረአበሮቹ፣ ተተኪዎቹ እና ተመዳቢዎች እንዲሁም የየራሳቸው ሠራተኞች፣ ወኪሎች፣ ዳይሬክተሮች እና ኃላፊዎች በሚከተለው ምክንያት ለሚደርስ ማንኛውም ኪሳራ ወይም ጉዳት ተጠያቂ አይሆኑም፦

ሀ) መተግበሪያውን፣ ድረ ገጹን ወይም አገልግሎቶቹን ማግኘት ወይም መጠቀም አለመቻል፤ ለ) በመተግበሪያው፣ በድረ ገጹ ወይም በአገልግሎቶቹ ላይ ልናደርጋቸው የምንችላቸው ማናቸውም ለውጦች፤ ሐ) በመተግበሪያው፣ በድረ ገጹ ወይም በአገልግሎቶቹ ላይ ያለ ማንኛውም ትክክል ያልሆነ ወይም ጉድለት ያለው ይዘት፤ መ) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሁሉም ጉዳዮች መተግበሪያውን፣ ድረ ገጹን ወይም አገልግሎቶቹን መጠቀም ባለመቻል የሚመጣ ማንኛውም የንግድ ወይም የትርፍ ኪሳራ።

3. በመተግበሪያው እና/ወይም ድረ ገጹ ላይ የሚደረጉ ለውጦች

DEAR ፋውንዴሽን መተግበሪያ እና/ወይም ድረ ገጹ በተቻለ መጠን ጠቃሚ እና ቀልጣፋ መሆኑን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ ነው። በዚህ ምክንያት፣ በመተግበሪያው እና/ወይም ድረ ገጹ ላይ ለውጦችን የማድረግ ወይም ለአገልግሎቶቹ በማንኛውም ጊዜ እና በማንኛውም ምክንያት ክፍያ የመጠየቅ መብታችን የተጠበቀ ነው። ለመተግበሪያው እና/ወይም ድረ ገጹ ወይም አገልግሎቶቹ ያለቅድመ ማስታወቂያ እና የክፍያ ምክንያት ማብራሪያ ሳንሰጥ አናስከፍልዎትም።  ለወደፊቱ፣ አገልግሎቱን ማዘመን እንፈልግ ይሆናል። ለመተግበሪያው በአሁኑ ጊዜ በአንድሮይድ እና በ iOS ላይ ይገኛል - የስርዓቶቹ መስፈርቶች ሊለወጡ የሚችሉ ሲሆን መተግበሪያውን መጠቀሙን ለመቀጠል ከፈለጉ ዝመናዎቹን ማውረድ ያስፈልግዎታል። DEAR ፋውንዴሽን ለእርስዎ ተዛማጅነት እንዲኖረው እና/ወይም በመሳሪያዎ ላይ በጫኑት ስሪት እንድሠሩ ሁል ጊዜ መተግበሪያውን እና/ወይም ድረ ገጹን እንደሚያዘምን ቃል አልገባም። ነገር ግን፣ ሁልጊዜ የመተግበሪያው ማሻሻያዎች ለእርስዎ ሲቀርቡ ለመቀበል ቃል ይገባሉ።

4. የአገልግሎት ጊዜ እና ማብቂያ

በእርስዎ እና በ DEAR ፋውንዴሽን መካከል ያለው ስምምነት በእርስዎ ወይም በእኛ እስኪቋረጥ ድረስ ተፈጻሚነት ይኖረዋል። በእኛ ምርጫ በማንኛውም ጊዜ እና በማንኛውም ምክንያት የመተግበሪያውን እና/ወይም የድረ ገጹን አገልግሎት ያለቅድመ ማስታወቂያ ልናግድ ወይም ልናቋርጥ እንችላለን። በሌላ መንገድ ካልነገርንዎት በቀር፣ በማንኛውም ማቋረጫ ጊዜ፣ (ሀ) በእነዚህ ውሎች ውስጥ የተሰጡትዎትን መብቶች እና ፈቃዶች ይቆማሉ፣ (ለ) መተግበሪያውን እና/ወይም ድረ ገጹን መጠቀም ማቆም አለብዎት፣ እንዲሁም (ከተፈለገ) ከመሳሪያዎ ላይ መሰረዝ አለብዎት። በተጨማሪም፣ የእነዚህን ውሎች ማንኛውንም ድንጋጌ ካላከበሩ፣ ማንኛውም ቅድመ ማስታወቂያ ከ DEAR ፋውንዴሽን ሳይሰጥ፣ አገልግሎቱ ወዲያውኑ ይቋረጣል። እርስዎም መተግበሪያውን እና ሁሉንም ቅጂዎቹን ከተንቀሳቃሽ መሳሪያዎ በመሰረዝ እና/ወይም ድረ ገጹን መጠቀም በማቆም ይህን ስምምነት ማቋረጥ ይችላሉ።

5. በውሎች እና ግዴታዎች ላይ የሚደረጉ ለውጦች

በእራሳችን ምርጫ እነዚህን ውሎች በማንኛውም ጊዜ የመቀየር ወይም የመተካት መብታችን የተጠበቀ ነው። ለውጦቹ በዚህ ገጽ ላይ ከተለጠፉ በኋላ ወዲያውኑ ተፈጻሚ ይሆናሉ።

6. ገዢ ህግ እና ስልጣን

እነዚህ ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲ የሚገዙት እና የሚተረጎሙት በስዊዘርላንድ ህጎች እና በEU አጠቃላይ የውሂብ ጥበቃ ደንብ መሰረት ነው። የስዊዘርላንድ ፍርድ ቤቶች በእነዚህ ውሎች እና በግላዊነት ፖሊሲ ወይም በእነርሱ በተቋቋመው ህጋዊ ግንኙነት ምክንያት የሚነሱ አለመግባባቶችን ለመፍታት ልዩ ስልጣን እንዳላቸው በማይለወጥ መልኩ ተስማምተዋል።

7. የቅጂ መብት

በሌላ መልኩ ካልተገለጸ በስተቀር፣ በመተግበሪያው እና/ወይም በድረ ገጹ ላይ ያሉ ሁሉም ቁሳቁሶች በ DEAR ፋውንዴሽን አዕምሯዊ ንብረት ውስጥ ናቸው። ከእኛ ግልጽ የጽሁፍ ፈቃድ ሳይኖር፣ ከግል እና ከንግድ ላልሆነ ዓላማ ውጭ፣ በማንኛውም ምክንያት የይዘታችንን ክፍል (ጽሑፍ፣ ምስሎች ወይም ቪዲዮዎች) ማባዛት፣ ማሻሻል ወይም ማከማቸት ህገወጥ ነው። ሁሉም ይዘቶች በአለምአቀፍ የቅጂ መብት ህግ የተጠበቁ ናቸው።

8. የተለያዩ

እነዚህ ውሎች እና ግዴታዎች እና ከግላዊነት ፖሊሲ የመተግበሪያ፣ የድረ ገጽ ወይም አገልግሎቶቹ አጠቃቀምዎን በተመለከተ የተገባውን ሙሉ ስምምነት ይይዛሉ እንዲሁም በእርስዎ እና በ DEAR ፋውንዴሽን መካከል ያለውን ማንኛውንም የቀድሞ ስምምነት ይተካሉ። በእነዚህ ውሎች እና ግዴታዎች ወይም የግላዊነት ፖሊሲ ውስጥ ያለ ማንኛውም ድንጋጌ ውድቅ፣ ህገወጥ ወይም ተፈጻሚነት የሌለው በሚሆንበት ጊዜ፣ የተቀሩት ድንጋጌዎች ትክክለኛነት፣ ህጋዊነት እና ተፈጻሚነት በምንም መልኩ ሊነኩ ወይም ሊበላሹ አይችሉም።

9. ያግኙን

ስለ ውሎቻችን እና ግዴታዎች ማንኛቸውም ጥያቄዎች ካሉዎት፣ በ  ላይ እኛን ለማግኘት አያመንቱ።

የመጨረሻው ዝመና፦ 22. ኤፕሪል 2021

ቋንቋዎን ይምረጡ

ይህ ድህረ ገጽ በድረ-ገጻችን ላይ ምርጡን ተሞክሮ እንያገኙ ኩኪዎችን ይጠቀማል |የግላዊነት ፖሊሲ